በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓረና የመንግሥት የፀጥታ አካላትን ከሰሰ


አቶ አብርሃ ደስታ
አቶ አብርሃ ደስታ

በመቀሌ ከተማ ኲሓ ክፍለከተማ ኲሓ በትናንትናው ዕለት በነበረው የፅዳት ዘመቻ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በአባላቶቼና በሌሎች ወጣቶች አካላዊ ጥቃት ተፈፅምዋል እንዲሁም ታሰሩ ሲል የዓረና ትግራይ ፓርቲ ከሰሰ።

የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ አብርሃ ደስታ እንደገለፁት እነዚህ ወገኖች ያሉበት ሁኔታ ለማየት የት እንዳሉ ለማወቅ አልቻልንም ሲሉ ተናገሩ።

የክፍለ ከተማው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ገብረክርስቶስ ገብረመስቀል የታሰሩት ሰዎች የአካባቢው ሰላም ለማወክ ስለተንቀሳቀሱና የፖሊሰ አባላትም ስለመቱ ነው በቁጥጥር ሥር ያዋልናቸው ብለዋል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎችም በክፍለ ከተማው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ

ዓረና የመንግሥት የፀጥታ አካላትን ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:31 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG