አብዮታዊ ዲሞክራስያዊ የአንድነት ግንባር የተባለው የአማጽያን ቡድን በአፋር ክልል በነበሩ ጎብኚዎች ላይ ባለፈው ሳምንት በከፈተው ጥቃት አምስት ጎብኝዎች ተገድለው ሁለት ጀርመናውያንና ሁለት ኢትዮጵያውያን እንደተጠለፉ የዜና ዘገባዎች መዘገባቸው ይታወሳል
የተጠለፉት ሰዎች በሽምግልና እንዲፈቱ ጥረት እንደተጀመረ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፓብሊክ ዲፕሎማሲ እና ኮሙኒኬሽንስ ዳይረክተር አቶ ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው አያይዘውም አርዱፍ የሚባለው ድርጅት የትጥቅ ትግሉን ትቶ በሀገሪቱ ህጋዊ በሆነመንገድ እየሰራ ነው። ይህ ቡድን ግን እንደተለመደው ኤርትራ የፈጠረቸው አካል ነው። የኢትዮጵያ ወታደሮች በአከባቢው ስላልነበሩም የተከፈተ ግጭት አልነበረም። ታጣቂዎች ሾልከው በመግባት በጎብኚዎቹ ላይ የጥይት እሩምታ ነው ያወረዱባቸው ሲሉ የአማጽያኑ ቡድን ጎብኚዎቹ የተገደሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ነው ላለው ምላሽ ሰጥተዋል።