በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዐረቡ ዓለም በአብዮት ማዕበል ውስጥ


የቀናቱ አብዮቶችና አንድምታቸው በባለሙያዎች ይገመገማሉ፡፡

ለውጥ ፈላጊው የቱኒዚያ ሕዝብ ባለፈው ሣምንት አደባባይ ወጥቶ ቁጣውን የገለፀበት የተቃውሞ ሠልፍ ፕሬዚደንቱን ቤን አሊን ከነቤተሰባቸው አገር ጥለው እንዲሸሹ አስገድዷል።

በግብፅ ተመሣሣይ ሕዝባዊ ቁጣ ተቀጣጥሎ ለ30 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየውን የፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባረክ መንግሥት አፍርሷል።

በሠላም ሥልጣን ካላስረከቡ ከቤን አሊ የተለየ ዕጣ እንደማይጠብቃቸው ግልፅ እየሆነ ነው።

በዮርዳኖስም በቱኒዚያና ግብፅ ሕዝቡ የመንግሥት ለውጥ ጥያቄ በማንሣት አደባባይ ወጥቷል።

በአገሪቱ እየናረ የመጣው የምግብ ዋጋና የባለሥልጣናቱ በሙስና መዘፈቅ አስቆጥቶታል።

ይህ በመካከለኛው ምሥራቅ እንደ ሰደድ እሳት እየተያያዘ ያለው ሕዝባዊ አመፅ ቀጥሎ ወዴት ያመራል?

በሌሎች የአፍሪቃ አምባገነን መንግሥታትስ ላይ ተመሳሳይ ሁኔታ ሊቀሰቅስ ይችል ይሆን?

ለወይይት ሁለት እንግዶችን ጋብዘናል። ዶክተር ጌታቸው መታፈሪያ በሜሪካንድ ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ መምህር ናቸው። አቶ ጁዋር መሐመድ ደግሞ የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅና በግጭቶችና ነፃ በሆኑ እቅስቃሴዎች ዙሪያ ምክር ለጋሽና መምህር ናቸው።

ያነጋገራቸው ሰለሞን ክፍሌ ነው፤ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG