በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአረብ ሀገራት በፍልስጥኤም ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ ያደረጉ የእስራኤል ጥቃቶችን አወገዙ


ፎቶ ፋይል፦ በደቡባዊ ጋዛ በደረሰ አየር ጥቃት ፍልስጤማውያን በህይወት የተረፉ ካሉ ፍለጋ እያደረጉ፤ ካን ዮኒስ እስራኤል፣ አአአ ጥቅምት 19/2023
ፎቶ ፋይል፦ በደቡባዊ ጋዛ በደረሰ አየር ጥቃት ፍልስጤማውያን በህይወት የተረፉ ካሉ ፍለጋ እያደረጉ፤ ካን ዮኒስ እስራኤል፣ አአአ ጥቅምት 19/2023

የአረብ ሀገራት፣ ሲቪሎችን ዒላማ ያደረገ ነው፤ ያሉትን የእስራኤል የጋዛ ጥቃት፣ ዛሬ አውግዘዋል፡፡

የውግዘቱን መግለጫ፣ ዛሬ ኀሙስ ያወጡት፡- የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ የዮርዳኖስ፣ የባሕሬን፣ የሳዑዲ አረቢያ፣ የኦማር፣ የኳታር፣ የኩዌት፣ የግብጽ እና የሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ናቸው፡፡

በእስራኤል ከባድ የቦምብ ድብደባ ሥር በምትገኘው ጋዛ፣ ሲቪሎችን ዒላማ ማድረግ እና “የዓለም አቀፉን ሕግ በጉልሕ መጣስ” ያሉትን የእስራኤል ድርጊት፣ ሚኒስትሮቹ በመግለጫቸው አውግዘዋል፡፡

እስራኤል፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን፣ በሐማስ ከተፈጸመባት ጥቃት በኋላ፣ ራስን እንደ መከላከል መብት በመቁጠር፣ የፍልስጥኤማውያንን መብት ችላ ማለቷ አግባብ እንዳልኾነ፣ የአረብ ሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ በመግለጫቸው ተችተዋል፡፡

በማዕከላዊ ጋዛ፣ የቡርጂ መጠለያ ካምፕ እና በምሥራቅ ቃራራ መንደር የሚገኙ ነዋሪዎች፣ እስራኤል ሌሊቱን ባደረሰችው የምድር ማጥቃት፣ ከባድ የታንክ ድብደባ ሲወርድባቸው ማደሩን ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG