በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የእስያ ፓሲፊክ አካባቢ አጋሮቻችን የማሪታይም ጸጥታቸው እንዲጎለብት እንረዳለን ሲሉ ቃል ገቡ


የአሜሪካ ድምጹዋ የዋይት ሃውስ (White House) ዘጋቢ ሜሪ ሳሊናስ (Mary Alice Salinas) የእስያ ፓሲፊክ የምጣኔ ሃብት ትብብር የመሪዎች ጉባዔ ከሚካሄድባት ከፊሊፒንስ ዋና ከተማ ማኒላ ያጠናቀረችው አጭር ዘገባ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የእስያ ፓሲፊክ አካባቢ አጋሮቻችን የማሪታይም (maritime)ጸጥታቸው እንዲጎለብት በሚካሄደው ባለው የዚህ ሳምንት ጉባዔ ተሳትፈዋል።

የአሁኑ የፕሬዚደንቱ ጉዞ ዩናይትድ ስቴትስ ከኣካባቢው ሃገሮች ጋር የንግድና የጸጥታ ትስስር በማጠናከር በክልሉ ያላትን ተሰሚነት ለማጎልበት የያዘችው ጥረት ኣካል ነው።

በጉባኤው ላይ የሃያ አንድ የክልላዊው ማህበር ኣባል ሃገሮች መሪዎች ይሳተፋሉ።

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አስቀድመው የፊሊፒንስን የባህር ሃይል መሪ መርከብ በጎበኙበት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ለደቡብ ምስራቅ እስያ አጋሮችዋ የማሪታይም ብቃታቸውን በዘመናዊነት ለማሳደግ እንዲረዳ የወጠነችውን በሁለት ዓመታት የሁለት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ዶላር አዲስ የጸጥታ ድጋፍ ዕቅድ ይፋ አድርገዋል።

“ይህ ጉብኝቴ የክልሉን የባህር ጸጥታ እና በባህሩ የመዘዋወር ነጻነትን ለማስከበር ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በአጽንዖት የሚመሰክር ነው” ብለዋል።

ቻይና በደቡብ ቻይና ባህር ክልል ላይ የያዘችው የይገባኛል አቁዋም የኣካባቢውን ሃገሮች ውጥረት ውስጥ መክተቱ ይታወቃል። የቻይና ፕሬዚደንት ጂ ጂንግ ፒንግ (Xi Jing Ping) በኣፔክ የመሪዎች ጉባኤ ላይ አንዱ ተሳታፊ ናቸው።

ራሱን የእስልምና መንግስት ብሎ የሚጠራው ቡድን ፈረንሳይ ፓሪስ ውስጥ ያደረሳቸ የሽብር ጥቃቶች በጉባዔው ኣጀንዳ ውስጥ ተይዙዋል።

የኣፔክ መሪዎች ስለሽብርተኝነትና ስለደቀነው ዓለም ኣቀፍ ስጋት የጋራ መግለጫ ያወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዝርዝሩን ቆንጂት ታዬ አቅባዋለች ከተያያዘው ይድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG