በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ አመጣጥ ላይ የተደረገው ጥናት ውጤት ድምዳሜ


የኮቪድ-19ን አመጣጥ በሚመለከት የዓለም የጤና ድርጅት እና ቻይና በጋራ ያካሄዱት አንድ ጥናት ስለኮሮናቫይረስ አመጣጥ ድምዳሜ ላይ መድረሱ ተጠቆመ።

የጋራ ጥናቱ ረቂቅ ውጤት እንደሚያሳየው "ከማናቸውም ይበልጥ የሚያሳምነው ኮሮናቫይረስ ወደሰው የተላለፈው ከሌሊት ወፍ በተጋባባቸው ሌሎች እንስሳት አማካኝነት ሳይሆን አይቀርም የሚለው ነው" የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን ነው አሶሼየትድ ፕሬስ የዘገበው።

ጥናቱ ቫይረሱ ከምርምር ላቦራቶሪ አምልጦ ወጥቶ ወደሰው ተላልፏል የሚለው እጅግ በጣም ሊሆን የማይችል ነው ማለቱን ኤፒ አያይዞ ዘግቧል። የድመት ዝርያዎች እና ሚንክ የሚሉዋቸው እንስሳትም ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ መሆናቸውንና የቫይረሱ ተሸካሚ ብሎም አዛማች ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥናቱ መጥቀሱንም አክሏል።

አሶሼየትድ ፕሬስ ይህን ረቂቅ የጥናት ውጤት ዛሬ ያገኘው የዓለም የጤና ድርጅት አባል ከሆነ ሃገር ዲፕሎማት መሆኑን ገልፆ፣ የዲፕሎማቶቹን ማንነት ግን የትናቱን ውጤት የማጋራት ፈቃድ ስላልተሰጣቸው ስማቸውን ይፋ አላደረገም።

ሪፖርቱ በአብዛኛው የተመረኮዘው በቅርቡ ዓለም አቀፍ የጤና አዋቂዎች ቫይረሱ መጀመሪያ ወደተነሳባት ወደቻይናዋ ዉሃን ከተማ ባደረጉት ጉብኝት ላይ መሆኑን አያይዞ ጠቅሷል።

XS
SM
MD
LG