በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታንዛኒያ መንግሥት ፖለቲካዊ ሰልፍ ማድረግ የሚያግደውን ሕግ አነሳ


ፎቶ ፋይል፦ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሳን
ፎቶ ፋይል፦ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሳን

የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሳን በአገሪቱ ለስድስት ዓመታት ተጥሎ የነበረውን ፖለቲካን በሚመለከቱ ጉዳዮች ሰልፍ ማድረግ የሚከለክለውን ሕግ አንስተዋል።

ከእርሳቸው ቀደም ብሎ የነበሩት ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሥልጣን ከያዙ በኋላ እአአ 2016 ፖለቲካን የተመለከቱ ሰልፎችን አግደው ነበር። ምክንያታቸውም ሰልፎቹ በቀላሉ ወደ ሁከት ያመራሉ የሚል ነበር።

የቪኦኤው ቻርለስ ኮምቤ ከዳር ኤስ ሳላም እንደዘገበው ፕሬዚዳንቷ ሳሚያ የሕጉን መነሳት ያስታወቁት ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ነው።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ከአንድ አመት በፊት በሞት ሲለዩ ወደ ሥልጣን የመጡት ሳሚያ ሃሳን የፖለቲካ ተቀናቃኝን ያፍናል ከሚባለው የማጉፉሊ ፖሊሲ እንደሚለዩ ለማሳየት በርካታ እርምጃዎችን ወስደዋል።

አንዳንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እንደሚሉት የፕሬዚዳንቷ እርምጃ በአገሪቱ ለሚገነባው ዲሞክራሲ የመሠረት ድንጋይ ሊሆን ይገባል።

ፕሬዚዳንት ሳሚያ ከዚህ በፊት ባደረጉት ንግግር በታንዛኒያ ዋና ዋና አንገብጋቢ ያሏቸውን ጉዳይችን አንስተው ነበር። በተለይም ዲሞክራሲንና እየጨመረ የመጣውን ለለዉጥ ያለውን ተስፋ በተመለከተ።

እነዚህን ለውጦች በተግባር ለማዋል ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችል የቪኦኤው ቻርለስ ኮምቤ ዘገባ አመልክቷል። ፕሬዚዳንቱ የተለየ አቀራረብ ቢኖራቸውም፣ እርሳቸውም ሆኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ዓባል ናቸው። በመሆኑም የፓርቲያቸው ድጋፍ ያሻቸዋል።

XS
SM
MD
LG