በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ


ለአምስት ቀናት የዘለቀውን የሶስት ሀገሮች ጉብኝታቸውን ትናንት ሴኔጋል ላይ ያጠናቀቁት ብሊንከን የባይደን አስተዳደርን የአፍሪካ ፖሊሲ ባስረዱበት ንግግራቸው ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ሃገሮችን በአቻ አጋርነት እንደምትመለከት ገልጸዋል
ለአምስት ቀናት የዘለቀውን የሶስት ሀገሮች ጉብኝታቸውን ትናንት ሴኔጋል ላይ ያጠናቀቁት ብሊንከን የባይደን አስተዳደርን የአፍሪካ ፖሊሲ ባስረዱበት ንግግራቸው ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ሃገሮችን በአቻ አጋርነት እንደምትመለከት ገልጸዋል

ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪካ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር የምታደርገው ጥረት የሚመዘነው በሚያስገኘው ውጤት ላይ ሊሆን ይገባል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ተናገሩ።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት ዩናይትድ ስቴትስ የሚበዛውን የውጭ ዕርዳታዋን ከተቀናቃኙዋ ከቻይና በምታገኘው አህጉረ አፍሪካ ያላትን የተደማጭነት ሚና ለማጎልበት የታለመውን ጉብኝታቸውን ትናንት ሲያጠናቅቁ በሰጡት ቃል ነው።

ለአምስት ቀናት የዘለቀውን የሶስት ሀገሮች ጉብኝታቸውን ትናንት ሴኔጋል ላይ ያጠናቀቁት ብሊንከን የባይደን አስተዳደርን የአፍሪካ ፖሊሲ ባስረዱበት ንግግራቸው ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ሃገሮችን በአቻ አጋርነት እንደምትመለከት ገልጸዋል።

ብሊንከን ትናንት ዳካር ላይ በተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ "የምንመዘነው በምንሰራው እንጂ እኔ በምለው ብቻ መሆን የለበትም ስለዚህ በቀጣዮቹ ወራት እና ዐመታት እንዴት ዐይነት ስራ እንደምንሰራ እንይ" ብለዋል ብሊንከን።

የሴኔጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አፍሪካ አይሳታ ቶል ሳል በበኩላቸው "የዩናይትድ ስቴትስ ተጽእኖ ሚና አፍሪካን ይጠቅማታል ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ ውስጥ ፈጽሞ ቅኝ ገዢ ሆና አታውቅም፤ ለእኛ ሴኔጋላውያንን ዩናይትድ ስቴትስን የነጻነት ሃገር ነች" ብለዋል።

አራት የዩናይትድ ስቴትስ ኩባኒያዎች ከሴኔጋል ጋር ባደረጉት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያለው ስምምነት ፊርማ ስነ ስርዐት ላይ የተገኙት ብሊንከን "ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ሀገሮች በኢንቨስትመንት ስትሰማራ ለመገመት የሚያዳግት ዕዳ ውስጥ አትከታቸውም" ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ትናንት ሴኔጋል ላይ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነትም ያነሱ ሲሆን በአፍሪካ ህብረት እና በአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኩ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ መሪነት እና በዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ የተያዘው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ጥረት ቀጥሏል ብለዋል። ባስቸኩዋይ ካለአንዳች ቅድመ ሁኒታ ተኩስ እንዲቆም እና ህይወት አድን ርዳታ ለሚያስፈልገው በሚሊዮኖች የተቆጠረ ህዝብ ሰብዐዊ ረዳኤት እንዲገባ ግፊት ማደረጋችንን ቀጥለናል ሲሉም አክለው ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ዳካር ላይ በሰጡት ቃል ከክሬምሊን ቤተ መንግሥት ጋር ግንኙነት ያለው በድብቅ የሚንቀሳቀስ የሩስያ ቡድን ማሊ ውስጥ የዲሞክራሲ ስርዐትን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም አስጠንቅቀዋል። ዋግነር ግሩፕ የተባለው የሩስያው ቡድን ማሊ ውስጥ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ መንግሥት እስከ መጭው ሚያዚያ በሚኖረው ጊዜ ውስጥ እንዲመሰረት ዐለም አቀፍ ድጋፍ ያለው ዕቅድ በተያዘበት በዚህ ወቅት ዋግነር ግሩፕ በሀገሪቱ ቢንቀሳቀስ አሳዛኝ ይሆናል ሲሉ አሳስበዋል።

ማሊ ለቀጣናው የወደፊት መረጋጋት ምሰሶ መሆኑዋን የምትቀጥል ሀገር ነች፥ እኛንም የአካባቢው መረጋጋት ጉዳይ እና ጽንፈኝነት እና ሽብርተኝነት እየተስፋፋ መሆኑ በጥልቅ ያሳስበናል ብለዋል።

ዋግነር ግሩፕ ቅጥር ተዋጊዎችን በሶሪያ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና በሊቢያ ያሰማራ ሲሆን ጉዳዩ ከምዕራባውያን እና ከሌሎችም በኩል ተቃውሞ አስነስቷል።

የሩስያው ፕሬዚደንት ቪላዲሚር ፑቲን የቅርብ አማካሪ የሆኑ ሰው ንብረት የሆነው ዋግነር ግሩፕ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ የሰብዐዊ መብቶችን በመጣስ እና በሊቢያው ጦርነት ውስጥ በመሳተፍ በምዕራባዊያን መንግሥታት እና በተ መ ድ ጠቢባን ተወንጅሏል

XS
SM
MD
LG