በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን አሜሪካ ድጋፏን እንደምትቀጥል ብሊንከን አስታወቁ


የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ለሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት ያቆመው የሰላም ስምምነት የተደረገበትን አንደኛ ዓመት ምክን ያት በማድረግ ባወጡት መግለጫ፣ በግጭቱ ሕይወታቸውን ያጡትን እንደሚያስቡ እና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰላም እና ፍትህ እንዲሰፍን ድጋፍ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

አሜሪካ “ከፍተኛ መሻሻል” አሳይቷል ያሉትን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በመልካም እንደምትቀበል እንዲሁም በትግራይ ግዜያዊ ክልላዊ አስተዳደር መቋቋሙን እና ሌሎችንም መልካም ያሉትን ለውጦች እንደምትደግፍ ብሊንከን ገልጸዋል።

አንዳድ ተግዳሮቶች አሁንም መኖራቸውን የጠቀሱት ብሊንክን፣ “ሕወሃት ከባድ መሣሪያውን ቢያስረክብም፣ በትግራይ ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ተጨማሪ ርምጃ ያስፈልጋል” ብለዋል።

የኤርትራ ኃይሎች ሙሉ ለሙሉ መውጣት እንዳለባቸው እና ኢትዮጳያም ሆነች ኤርትራ በቀጠናው የሚገኙ ሀገራትን ሉአላዊነት ማክበር እንዳለባቸው ብሊንከን አሳስበዋል።

በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች እንደሚያሳስቧቸው ብሊንከን ገልጸዋል።

የሰላም ስምምነቱን ቀሪ አፈጻጸም አሜሪካ መደገፏን እንደምትቀጥልም ብሊንከን በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG