በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃውሞ ሰልፍ በቤይሩት


በቤይሩት ተቃውሞ ሰልፍ
በቤይሩት ተቃውሞ ሰልፍ

ሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ከ137 በላይ ሰዎች የገደለው ከባድ ፍንዳታ ያስቆጣቸው ተቃዋሚ ሰልፈኞች ትናንት ማታ ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል።

መሃል ቤይሩት የሚገኘው ፓርላማው ደጃፍ የተሰባሰቡትን ተቃዋሚዎች አድማ በታኝ ፖሊሶች የበተኑዋቸው ሲሆን ተቃዋሚዎች መሃል አንዳንዶቹ ፖሊሶቹ ላይ ድንጋይ ወርውረዋል ቁሳቁስችንም በእሳት ለኩሰዋል።

ብዙዎች ሊባኖሳውያን ፍንዳታው የደረሰው በፖለቲካ ልሂቃኑ ሙስናና እና የአስተዳደር ብልሹነት ነው ሲሉ ቁጣቸውን ገልጸዋል።

ትናንት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ብዙዎች ነዋሪዎች በሊባኖስ መንግሥት ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል።

የእርዳታ መዋጮ እንዲሰበሰብ ዓለምቀፍ ጉባዔ አዘጋጃለሁ ያሉት ማክሮን የፖለቲካ መሪዎቹን የፈለጋችሁትን አድርጉበት ብሎ ቼክ የሚሰጣችሁ ግን የለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ቤይሩት እንድታገግም የሚሰጥ እርዳታ ከአዲስ የፖለቲክ ሥርዓት መመስረት ጋር ይቆራኛል ያሁኑ የህዝብ አመኔታ የለውምና ሲሉም ማክሮን አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG