በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ወደ አንጎላ እና ጀርመን ሊያደርጓቸው የነበሩ ጉዞዎችን አዘግይተዋል


የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን

የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ኬረን ጃን ፒየር በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ፤ በሀገር ውስጥ ሄሪኬይን ሚልተን የተሰኘው ከአውሎ ንፋስ ጋር የተቀላቀለው ዝናብ ሊያደርሰው ከሚችለው አደጋ ስጋት አኳያ፤ በተጨማሪም ባለፉት ሳምንታት ኼሪከን ሄለን በደቡብ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ ላስከተለው ጉዳት ዝግጅትና ምላሽ ለማድረግ ፕሬዘዳንቱ ወደ ጀርመን እና አንጎላ ሊያደርጉ ይዘዋቸው የነበሩ የጉዞ እቅዶችን ማራዘማቸውን አመልክተዋል፡፡

ባይደን በፕሬዘዳንትነንት ዘመናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አፍሪካዊቷ ሀገር አንጎላ ሊያደርጉ ይዘውት የነበረው ዕቅድ በነዳጅ ዘይት ሃብቷ የላቀችው አንጎላ ዩናይትድ ስቴትስ ከቻይና በተቃራኒው በአፍሪካ የያዘችውን ግዙፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እና በሀገሪቱ ላይ ያላትን ትኩረት ያመላከተ ነው፡፡

የመጀመሪያቸው በሚሆነው የአፍሪካ ጉዟቸው አንጎላን ቀዳሚ አድርገው መምረጣቸው፤ በነዳጅ የበለጸገችው ሀገር በአሜሪካ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ትኩረት የተሰጣትን ስፍራ እና ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ የቻይናን ኢንቨስትመንቶች በሚገዳደር መልኩ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ተመላክቷል፡፡

ባይደን የስራ ዘመናቸው ሊያበቃ ጥቂት ወራት ሲቀሩት ከመጭው እሁድ እስከ ማክሰኞ ድረስ ሊያደርጉት አቅደውት የነበረው የጉብኝት መርሃ ግብር በማዕድን የበለፀጉ የአፍሪካ ሀገራትን ከአንጎላ የአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደብ ሎቢቶ ጋር የሚያገናኘውን 1300 ኪሎ ሜትር የባቡር ሀዲድ የሚያድስ ግዙፍ ብሔራዊ ፕሮጀክትን ያካተተ ነበር፡፡

የሎቢቶ ኮሪደር የሚሰኘው እና በጎሮጎርሳዊያኑ 2026 እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው ይኸው ፕሮጀከት፤ ከዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ዛምቢያ የማዕድን ማውጫዎች የሚመጡ መዳብ እና ኮባልት ማዕድናትን ጨምሮ ለአለም ምጣኔ ሀብት ቁልፍ የሆኑ ማዕድናትን ለማጓጓዝ ቁልፍ የሆነ ፕሮጄክት ነው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG