በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፕሬዚዳንት ዣኦ ሎሬንኮ ሥልጣን ዘመን በአንጎላ ሙስና መቀነሱ ተጠቆመ

የአንጎላው ፕሬዚዳንት ዣኦ ሎሬንኮ
የአንጎላው ፕሬዚዳንት ዣኦ ሎሬንኮ

የአንጎላው ፕሬዚዳንት ዣኦ ሎሬንኮ ከአንድ ዓመት ባላይ በሆነው የሥልጣን ጊዚያቸው ሙስናን ለማቆም ባደረጉት ጥረት ካለፉት የሀገሪቱ አስተዳደሮች የተሻለ ስኬት አስገኝተዋል ሲሉ መንግሥቱን አጥብቀው የሚነቅፉት ሳይቀሩ ተናግረዋል።

የአንጎላው ፕሬዚዳንት ዣኦ ሎሬንኮ ከአንድ ዓመት ባላይ በሆነው የሥልጣን ጊዚያቸው ሙስናን ለማቆም ባደረጉት ጥረት ካለፉት የሀገሪቱ አስተዳደሮች የተሻለ ስኬት አስገኝተዋል ሲሉ መንግሥቱን አጥብቀው የሚነቅፉት ሳይቀሩ ተናግረዋል።

ሎሬንኮ ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ ሥልጣን የያዙት የረዥም ጊዜ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆሴ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ጡረታ ከወጡ በኋላ ነበር። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቤተሰቦችና ወዳጆች እያንዳንዱን ወሳኝ ኩባንያንና የሀገሪቱን የኃብት ምንጮችን ይቆጣጠሩ እንደነበር ተዘግቧል።

ሎሬንኮ ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ግን በዶስ ሳንቶስ አስተዳደር ወቅት የማይነኩ ተደርገው ይታዩ የነበሩት በርካታ ከፍተኛ ባለሥልጣኖችን እንደጠራረጉ ታውቋል። ዋናው ተጠቃሽ ምሳሌ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ልጅ ፊሎሜኖ በገንዘብ ማጭበርበርና በገንዝብ ዝውውር ተከሰው በያዝነው ሳምንት ታስረዋል። ሶቨሪን ዌልት ፋንድ የተባለውን ባንክ ይመሩ ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG