በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ መሪዎች ስለ ኮንጎ ደኅንነት ለመነጋገር በአንጎላ ተሰበሰቡ


የአፍሪካ መሪዎች ስለ ኮንጎ ደኅንነት ለመነጋገር በአንጎላ ተሰበሰቡ
የአፍሪካ መሪዎች ስለ ኮንጎ ደኅንነት ለመነጋገር በአንጎላ ተሰበሰቡ

የአፍሪካ መሪዎች እና በርካታ የክልላዊ ተቋማት ባለሥልጣናት፣ ዛሬ በአንጎላ ተሰብስበው፣ በምሥራቅ ዴሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች በሚፈጽሟቸው ጥቃቶች ሳቢያ፣ በተከሠተው የደኅንነት ቀውስ ላይ ተወያይተዋል፡፡

“እዚኽ የተሰበሰቡት ሁሉም ድርጅቶች፣ አንድ ዓይነት ተልዕኮ አላቸው፤” ያሉት የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንኮ፣ ዓላማው፥ “የታላቁን ሐይቅ አካባቢዎች ከግጭት ማጽዳት” እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አያይዘው እንደተናገሩት፣ “ግጭቶቹ፣ በማይጠገን ኹኔታ የልማት ዕቅዶችን ሲያዘገዩ፣ ተፈላጊውን ክልላዊ እና አህጉራዊ የመዋሐድ አጀንዳዎችንም አደጋ ላይ እንደጣሉ በሰፊው ይታወቃል፤” ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በበኩላቸው፣ “የአካባቢውን ሰላም እና ደኅንነት ወደነበረበት ለመመለስ፣ ያለንን ቁርጠኛ መርሖ በማክበር፣ ለታላላቅ ፕሮጀክቶቻችን በመታመን ጠመንጃዎችን ጸጥ ማድረግ፣ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፤” ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

እዚኽ የተሰበሰቡት ሁሉም ድርጅቶች፣ አንድ ዓይነት ተልዕኮ አላቸው፤”

የኅብረቱ ሊቀ መንበር አክለውም፣ አራት ወገኖች በተገናኙበት በዚኽ ስብሰባ፣ ኮንጎ ሰላሟ እና ደኅንነቷ የተረጋገጠ፣ እንዲሁም የበለጸገች አገር እንድትኾን መፍትሔ ለማፈላለግ፣ በንቃት አስተዋፅኦ እንድናደርግ፣ የሐሳብ እና ልምድ ልውውጣችንን ማጠናከር ይኖርብናል፤ ብለዋል፡፡ ይህንም ለማሳካት፣ ተገቢ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና የደኅንነት መፍትሔዎችን ማስቀደም እንደሚገባ ሊቀ መንበሩ መናገራቸውን፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በስብሰባው ላይ፣ የቡሩንዲ፣ የዚምባቡዌ፣ የጋቦን፣ የዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ የሩዋንዳ፣ የኮሞሮስ፣ የናምቢያ መሪዎች፣ እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮች መገኘታቸው ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG