በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒኩሌር የጦር መሣሪያዎቿን በማስወገድ - ሰሜን ኮሪያ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ኒኩሌር የጦር መሣሪያዎቿን በማስወገድ ሃሣብ እንደማትገፋ ሰሜን ኮሪያ አስታውቃለች።

ኒኩሌር የጦር መሣሪያዎቿን በማስወገድ ሃሣብ እንደማትገፋ ሰሜን ኮሪያ አስታውቃለች።

ፒዮንግያንግ ባለፈው ሣምንት ውስጥ ባወጣችው መግለጫ መርኃግብሯን እንድታቆም በቅድሚያ “የኒኩሌር ሥጋት” ስትል የጠራችውን ዩናይትድ ስቴትስ በአካባቢው የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንድታስወግድ አሳስባለች።

የሃገሪቱ መግለጫ እንዳስደነገጣቸው የገለፁት የሰሜን ኮሪያ ጥናቶች ተቋም ኃላፊው ዮንግዉክ ሪዩ ኒኩሌር የጦር መሣሪያዎችን በማስወገድ ጉዳይ ላይ “ዩናይትድ ስቴትስና ደቡብ ኮሪያ በአንድ ወገን በሌላው ደግሞ ደቡብ ኮሪያ ያላቸው ግንዛቤ የተለያየ መሆኑን ብዙ ሰው ቀድሞም ጠርጥሯል” ብለዋል።

ኒኩሌር የጦር መሣሪያዎችን ማስወገድ ሲባል ሰሜን ኮሪያ የምትረዳው የዩናይትድ ስቴትስን ኃይሎች ከኮሪያ ልሣነ-ምድር ማስወጣትና የዩናይትድ ስቴትስን የኒኩሌር ሥጋት ማስወገድን ነው ብለዋለ ሪዩ።

“ኒኩሌር የጦር መሣሪያዎችን ማስወገድ” የሚለውን “በዩናይትድ ስቴትስና በደቡብ ኮሪያ የተፈጠረ አባባል ፒዮንግያንግ ቀምታቸዋለች” ያሉት የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ሪዩ ሰሜን ኮሪያ በዚህ ጊዜ ምንም ዓይነት ድርድር የመጀመር ሃሣብ ያላት እንደማይመስላቸው ጠቁመዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ አንድ ካንሳስ ግዛት ውስጥ ከሚገኝ ራዲዮ ጋር ባለፈው ሣምንት ውስጥ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ኒኩሌር የጦር መሣሪያዎችን በማስወገድ አፈፃፀም ጉዳይ ላይ “ከሊቀመንበር ኪም ጆንግ ኡን ጋር እየሠራን ነን” ብለው ነበር።

“ፕሬዚዳንት ትረምፕ እና ሊቀመንበር ኪም በመጭው የአውሮፓ አዲስ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ለመነጋገር እንደገና ይገናኛሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓምፔዮ ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG