በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንታዊ እሰጥ አገባ በአሜሪካ - የምሁር ትንተና


ክርክሩ የብዙዎችን ቀልብና ልቦና ስቦ አልቋል፡፡ ቀደም ሲል ታስቦ እንደነበረውም በተመልካች ብዛት በአሜሪካ የቴሌቪዥን ታሪክ አቻ እንዳልነበረው ተዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንታዊ እሰጥ አገባ በአሜሪካ - የምሁር ትንተና
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:20 0:00
በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ እሰጥ አገባ ላይ ከዶ/ር ብሩክ ኃይሉ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:47:35 0:00

የሰኞ ምሽቱ የዕጩ ፕሬዚዳንቶች ክርክር ዋና ዋና በሚባሉ የአሜሪካ ቴሌቪዥን ጣቢያዎችና በብዙ የራዲዮ ሥርጭቶች በቀጥታ ተላልፏል፡፡

በተመልካች ብዛትም ክብረወሰን የሰበረ ተብሏል፡፡

ከመቶ ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን በቀጥታ እንደሚመለከቱት ቀደም ሲል ተተንብዮ ነበር፡፡

የበሰሉት ፖለቲከኛ ሂላሪ ክሊንተን በዚያ ግጥሚያ ያሸንፋሉ ብሎ ቀድሞ የገመተው መራጭ ከ65 ከመቶ በላይ ሲሆን ወደ ፖለቲካው ዓለም ዘው ብለው የገቡት እንዲያውም በራሣቸው ፓርቲ አባላት፤ በሪፐብሊካኖቹ የውጭ ሰው ወይም ባይተዋሩ እየተባሉ የሚጠሩት ነጋዴ ዶናልድ ትራምፕ በትንቅንቁ ብዙም የሚያጠረቃ ውጤት አያመጡም ሲሉ ብዙዎች ቀድመው ተናግረዋል፡፡ እንዲያውም ከ35 ከመቶ ያነሠ መራጭ ነው እሰጥ አገባውን እርሣቸው በድል ይወጡታል ያለ፡፡

ሁለቱም ዕጩዎች፤ አንዱም ፕሬዚዳንታዊ አይደሉም፤ ሌላዪቱም መታመን የላቸውም እየተባሉ ጥርጣሬ ተጥሎባቸው ቆይተዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ሰሞኑን ብዙ ዘመቻ ሲያደርጉ ነው የሰነበቱት፡፡ ሂላሪ ክሊንተን ለተወሰኑ ቀናት ታምመው፤ እቤትም ውለው ነበር፡፡

ለአንድ ሰዓት ተኩል የተካሄደው ክርክር በአሜሪካ የዛሬ ሁኔታ ላይ፣ በሥራ ፈጠራ፣ በንግድ፣ በግብር ጉዳዮች ላይ፣ በአሜሪካዊያን መካከል ባለው ግንኙነት ላይ፣ በሽብር ፈጠራና የአሜሪካን ደኅንነት በመጠበቅ ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ልውውጦችና እንካ ሰላንቲያ ተነስቶበታል፡፡

ክርክሩ የብዙዎችን ቀልብና ልቦና ስቦ አልቋል፡፡ ቀደም ሲል ታስቦ እንደነበረውም በተመልካች ብዛት በአሜሪካ የቴሌቪዥን ታሪክ አቻ እንዳልነበረው ተዘግቧል፡፡

የክርክሩን ይዘትና አካሄድ የተለያዩ የፖለቲካ ሣይንስ ምሁራን በተለያየ መንገድ ያዩታል፡፡

በኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ የስክሪፕስ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት መምህርና የፉልብራይት ስኮላር፣ እንዲሁም በዲፕሎማሲው መስክ እስከ ምክትል አምባሣደርነት ያገለገሉት የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር ዶ/ር ብሩክ ኃይሉ ሃሣባቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አድማጮች አካፍለዋል፡፡

ለዘገባውና የሙሉው ቃለ-ምልልስ የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG