የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኅዳር ወር መጨረሻ የተመዘገበው የዋጋ ንረት 16.9 በመቶ መኾኑን ገልጾ፣ “ይህም ባለፉት አምስት ዓመታት ከተመዘገበው ዝቅተኛው ነው” ሲል ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ባንክ አዲስ የተቋቋመው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የመጀመርያ ስብሰባን ተከትሎ በአወጣው መግለጫ ለዚህ ውጤት መገኘት ደግሞ የተከተለው ጥብቅ የገንዘብ ቁጥጥር ፖሊሲ ዋና ምክንያት መሆኑን ገልጿል።
የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የፋይናስ ባለሞያዎች በበኩላቸው መንግሥት አሁንም የዋጋ ንረቱን ከዚህም በላይ ዝቅ ለማድረግ መሥራት ይኖርበታል ብለዋል። ባለሞያዎቹ፣ “የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ ነው ማለት ኑሮ እየረከሰ ነው ማለት አይደለም” ብለዋል። በዚኽ ዙሪያ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም