በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል የጦርነቱ ወቅት እስረኞች እንዲፈቱ ውሳኔ አሳለፈ


የትግራይ ክልል የጦርነቱ ወቅት እስረኞች እንዲፈቱ ውሳኔ አሳለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:19 0:00

የትግራይ ክልል የጦርነቱ ወቅት እስረኞች እንዲፈቱ ውሳኔ አሳለፈ

የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ተከትሎ፣ በትግራይ ክልል፥ “ከጠላት ጋራ ተባብራችኋል፤ የምከታ ሒደቱን አደናቅፋቹኋል፤” የሚሉትን ጨምሮ፣ 30 በሚደርሱ የክሥ ዝርዝሮች ተከሥሠው በእስር ላይ የቆዩ ግለሰቦች እንዲፈቱ፣ የክልሉ አስተዳደር ወሰነ፡፡

ውሳኔው፣ ከቅዳሜ፣ ሚያዝያ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚኾን፣ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ሓላፊ አቶ ሓዱሽ ተስፋ ተናግረዋል::

በተዘረዘሩት ክሦች የታሰሩ ሰዎችን ትክክለኛ ብዛት አስመልክቶ፣ የተጣራ መረጃ እንደሌላቸው ሓላፊው ጠቅሰው፣ በቅርቡ፣ መረጃ በማሰባሰብ ሁነኛ ቁጥር ቁጥር ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡን፣ የዓረና ለዴሞክራሲ እና ለሉዓላዊነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ዓምዶም ገብረ ሥላሴ፣ ከክሦቹ ዝርዝር ጋራ በተያያዘ፣ በክልሉ፣ በ10ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረው ሊኾን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

አቶ ዓምዶም፣ እነዚህ ሰዎች፣ “ቀድሞውንም መታሰር የሚገባቸው አልነበሩም፤” ሲሉ፣ የእስራቸውን መነሻ ተችተው፣ በተለይ ደግሞ፣ ከፕሪቶርያው ስምምነት በኋላ ወዲያው ሊፈቱ ይገባ እንደነበር አክለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG