በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለስደት መንግሥት ሃሣብ


ENTC and EYNM - Emblems
ENTC and EYNM - Emblems

ስለስደት መንግሥት ሃሣብ - /ርዝመት 6ደ 55ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:55 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያ የስደት መንግሥት አደራጅ ኮሚቴ በሚል ስም የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ አንድ የስልክ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅተው ነበር፡፡

የመግለጫቸው ዓላማ የስደት መንግሥት ምሥረታ ሂደትና ተያያዥ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ መስጠት መሆኑን አሳውቀው ነው ወደ ገለፃቸው የዘለቁት፡፡

መስከረም 1/2008 ዓ.ም የጠሩት ጋዜጣዊ ጉባዔ አደራጆች ቀደም ባሠራጯቸው ፅሁፎች “ከኢትዮጵያ የስደት መንግሥት ምሥረታ አስተባባሪ አባል ተቋማትና ድርጅቶች መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሱት ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ነኀሴ 15/2007 ዓ.ም የስደት መንግሥቱን የመመሥረት ሂደት መጀመራቸውን ይፋ አድርገዋል” ይላል፡፡

በመግለጫው የኢትዮጵያ የስደት መንግሥት የመጨረሻ ግብ “ኢትዮጵያ ውስጥ የተረጋጋና ወደ ዘለቄታዊ ሠላም የሚያመራ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር መኖሩን ማረጋገጥ ነው” ብለዋል አደራጆቹ፡፡

በዚህ የስልክ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አውስትራሊያ፣ ቤልጅየም፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሣይ፣ ጀርመን፣ እሥራኤል፣ ጣልያን፣ ኬንያ፣ ሆላንድ፣ ኖርዌይ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስዊድን፣ ስዊትዘርላንድ፣ እንግሊዝ እና ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖር ብዙ ሰው መጋበዙንና መሣተፉንም አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

ወደ ቴሌ ኮንፍራንሱ የገቡ ጋዜጠኞች ላነሷቸው ጥያቄዎች የአዘጋጆቹ ድርጅቶች መሪዎች መሆናቸው የተገለፀው አቶ ስለሺ ጥላሁን እና አቶ ስዩም ወርቅነህ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ለመንደርደሪያው አጭር ዘገባ ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG