በኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ ያስፈልጋል? ለምን? ከፖለቲካ ድርጅቶች ምን ይጠበቃል? ከህዝብስ?
ጥያቄዎቻችሁን እንዲመልሱ በህግና ብሔራዊ እርቅ ዙሪያ ፅሑፎች ያበረከቱና የሥራ ልምድ ያላቸው ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጋብዘናል።
ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማሪያም በርዋንዳ ለተካሄደው የጅምላ ፍጅት የዓለምአቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ህግ ሆነው ያገለገሉ የህግ ባለሙያ ናቸው። ዶክተር ብርሃኑ መንግሥቱ ደግሞ በዩናይትድ ስቴትስ፤ ቨርጂንያ ኦልድ ዶሚኒየን ዩኒቨርሲቲ የንግድና ህዝባዊ አስተዳደር መምህር ናቸው። በድርድርና ብሔራዊ እርቅ ላይ ጥናት አካሄደዋል፡፡ በብሔራዊ እርቅ ዙሪያ በርካታ ፅሑፎችን አበርክተዋል። እነሆ ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ይሰጣሉ፤ የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ትዝታ በላቸው ናት።
ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡