ዋሺንግተን ዲሲ —
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለምቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ያወጣው ዓመታዊ ዘገባ ወደ 160 በሚጠጉ ሀገሮች ተፈፀመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ አስፍሯል።
ያለፈው 2017 በዓለም ደረጃ አንዳንድ እጅግ ኃያል የሆኑ መሪዎች እንዲዘወተር ያዳረጉት የጥላቻና የፍርሀት ፖለቲካ ተንፀባርቆበታል ይላል ዘገባው።
አዲሱ የአምነስቲ ዘገባ የግብፅ፣ የፊሊፒንስ፣ የቬኒዝዌላ፣ የቻይና፣ የሩስያና የዩናይትድ ስቴትስ መሪዎች በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሰብዓዊ መብት እንደሸረሸሩ ይገልፃል። የሰብዓዊ መብት ህጎችን በግላጭ ጥሰዋል፤ ወይም ሌሎች የሰብዓዊ መብት ህግን እንዲጠሱ ጥሪ ያደርጋሉ።
የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ዱተርቴማ ሰዎች በአደንዛዥ ዕፅ ንግድ የሚጠረጠሩትን እንዲገድሉ ጥሪ አድርገዋል ሲሉ የአምነስቲ ዋና ስራ አስኪያጅ ማርግሬት ሁኣንግ ጠቁመዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፍልሰት ጉዳይ ላይ ያቸውን አቋም፣ የፕሬስ ነፃነትን በመሸርሸርና በሴቶች መብት ላይ ባላቸው አመለካከት ዘገባው ነቅፏቸዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ