በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የቦኮ ሀራም ቡድን በናይጄሪያና በካሜሩን ከ4መቶ በላይ ሲቪሎች ገድሏ" - አምነስቲ ኢንተርናሽናል


“ነውጠኛው እስላማዊ ቡድን” ቦኮ ሀራም ካለፈው ሚያዝያ ጀምሮ ናይጄሪያና ካሜሩን ውስጥ ባካሄደው ጥቃት፣ ወደ 4መቶ ሲቪሎች በአጥፍቶ ጠፊ ቡድኖች መገደላቸውን፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

“ነውጠኛው እስላማዊ ቡድን” ቦኮ ሀራም ካለፈው ሚያዝያ ጀምሮ ናይጄሪያና ካሜሩን ውስጥ ባካሄደው ጥቃት፣ ወደ 4መቶ ሲቪሎች በአጥፍቶ ጠፊ ቡድኖች መገደላቸውን፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

ይህ በዚህ ዓመት ብቻ የተካሄደ ጥቃት ሲሆን፣ ባለፉት አምስት ወራት ከነበረው ከእጥፍ በላይ እንደሆነም ታውቋል።

ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ቡድን አምነስቲ ዛሬ ማክሰኞ ይፋ ባደረገው በዚህ ሪፖርቱ እንዳመለከተው፣ በነሐሴ ወር የተገደሉትን መቶ ሲቪሎችን ጨምሮ ካለፈው ሚያዝያ ወር ወዲህ 2መቶ ሃያ ሦስት ሲቪሎች የተገደሉት በቦኮ ሀራም እጅ ነው።

ከፍተኛ የደም መፋሰስ የተፈፀመበት ጥቃት የተካሄደው፣ እአአ ባለፈው ሐምሌ 25 ቀን 40 ሰዎች ቦርኖ ውስጥ በሚገኝ የነዳጅ ማውጫ ላይ ፍንዳታ በተደረገበት ጊዜ መሆኑም ታውቋል።

በጎረቤት ካሜሩን ደግሞ ካለፈው ሚያዝያ ወር ወዲህ ቢያንስ 1መቶ ሃምሳ ስምንት ሲቪሎች በ30 የተለያዩ አጥፍቶ ጠፊዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ሌሎች 16 ሲቪሎችም ዋዛ ውስጥ በተመሳሳይ ጥቃት ሕይወታችው አልፏል።

በእነዚህ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች የሚፈፀመው ግድያ ከፍተኛውን አኃዝ ያስመዘገበ መሆኑን ያመለከተው አምነስቲ፣ ብዙውን ጊዜ አጥፍቶ ጠፊዎቹ በቦኮ ሀራም የሚመለመሉ ሴቶችና ህፃናት ናቸው ብሏል።

የቦኮ ሀራምን ጥቃት ሽሽት፣ ወደ 2.3 ሚሊዮን ሕዝብ ከናይጄሪያ፣ ከካሜሩን፣ ከቻድና ከኒዠር የተሰደዱ ሲሆን፣ ከነዚሁ ውስጥ ወደ 7 ሚሊዮን ያህሉ፣ ለከፋ ረሀብና የመግብ እጥረት የተጋለጡ ናቸው ብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG