በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአምነስቲ ክስ በግብፅ ላይ


የግብፅ መንግሥት በጋዜጠኞችና በሌሎችም የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሰ።
የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን የፕሬስ ቀንን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት "ይህ በመገናኛ ብዙኃን ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት የጋዜጠኞችን የመናገርና ሃሣብን የመግለፅ መብት የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ህብረተሰብም መረጃዎችን ከነፃ አካላት እንዳያገኝ የሚገደብ እርምጃ ነው" ብሏል።
በተለይም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ውስጥ ሃሣብን መግለፅና መረጃን ምንጮች ማግኘትን ማረጋገጥ የሕዝብን መታመን ለማትረፍና የተሳሳቱ መረጃዎችንም ለመዋጋት እጅግ ቁልፍ ጉዳይ ነው አምነስቲ።
አንድ ጋዜጠኛ በግል የፌስቡክ ገፁ ላይ በመንግሥቱ የኮቪድ-19 ቁጥሮች ላይ ጥያቄ በማንሳቱ መታሠሩንና ያለበት ቦታም እንደማይታወቅ አምነስቲ ገልጿል። ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ የግብፅ መንግሥት በአሥሮች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞችንና ሌሎችም የመገናኛ ብዙኃን ባልደረቦችም ሥራቸውን እያከናወኑ በመሆናቸው ብቻ በሕግ ጣሾች ዝርዝር ውስጥ አስገብቷቸዋል ብሏል የአመነስቲ መረጃ። የግብፅ መንግሥት አስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

XS
SM
MD
LG