በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አምነስቲ ለኢትዮጵያ ፓርላማ ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ።


Amnesty International Logo
Amnesty International Logo

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ለኢትዮጵያ ፓርላማ አባላት ግልጽ ደብዳቤ ልኳል። የምክር ቤቱ አባላት ነገ አርብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ለመምከር እየተዘጋጁ ባሉበት በዚህ ወቅት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ይበልጥ እንዲያስቡ ጥሪ እናቀርባለን፤ ብሏል።

በነገው የፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዙሪያ ክርክር የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አብይ ትኩረት እንዲሆን ነው፤ አምነስቲ በግልጽ ደብዳቤው የጠየቀው።

የኢትዮጵያ ፓርላማ አዲሱ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀድሞውንም የጠበበውን በሃገሪቱ ያለውን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት፤ የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብቶች ይበልጥ እንዳያጠፋ ማረጋገጥ አለበት” ሲል የሚንደረደረው የአምነስቲ መግለጫ የብሔራዊው ሸንጎ በነገው ዕለት ሲከፈት አባላቱ በሚያደርጉት ክርክር ወቅት፤
“አሳሳቢውንና የከፋውን” የአገሪቱን ሁኔታ በቅጡ እንዲያጤኑ አሳስቧል።

“አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው” ሲሉ፤ የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር ሳሊ ሼቲ ለፓርላማ አባላቱ በላኩት ደብዳቤ “መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ” ያሉበትን አቶ ፍስሃ ያብራራሉ። ይበልጥ የሚያሳስበን ደግሞ የጸጥታ ኃይሎች አስፈላጊ ያሉትን ኃይል እንዲጠቀሙ መታዘዙ ነው፤ ይላሉ አቶ ፍስሃ።

“ሁላችሁም” ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ዋቢ ያደረገው የአምነስቲ መግለጫ፤ (የፓርላማ አባላትም ጭምር ማለታቸው ነው) “ሁላችሁም በሕግ እንድተዳደሩ፤ የሕዝቡን ፍቃድ እንድታከብሩና ለሕሊናችሁ እንድትገዙ፤ የሃገሪቱ ሕገ-መንግስት ግድ ይጠይቃል።

በአስቸኳይ አዋጁ ጉዳይ ውሳኔ በምትታሳልፉበት ወቅት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብዓዊ መብት መከበር ሙሉ ትኩረት መስጠት በእጅጉ አስፈላጊ ነው።” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG