በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሶርያ ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ


የቱርክ ወታደራዊ ኃይሎች እና በቱርክ የሚደገፍ የሶርያ ታጣቂ ቡድኖች በሰሜን ምሥራቅ ሶርያ ውስጥ በከፈቱት ጥቃት “የሲቪሎችን ሕይወት አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ፣ ክብር አሳጥቶታል” ሲል ዓለምቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ውግዘት አሰማ፡፡

“የበረቱ የሕግ ረገጥዋችና የጦር ወንጀሎች፣ ጅምላ ግድያዎችና ሲሚሎችን የገደሉና ጉዳት ያደረሱባቸው ሕገወጥ ጥቃቶች” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥፋት ያላቸውን አድራጎቶች ዘርዝሯል፡፡

የአምነስቲ ሪፖርት የተመረኮዘው የጤናና የፈጥኖ ደራሽ ዕርዳታ ሰጭዎች፣ የተፈናቀሉ ሲቪሎች፣ ጋዜጠኞችና ሰብዓዊ ድጋር አድራሾች የሚገኙበትን ቡድን ያቀፈ 17 ሰዎችን እማኝነት መሆኑን - ጠቁሟል፡፡

መኖሪያ ቤት፣ ዳቦ መጋገሪያ፣ ትምህርት ቤትን ጨምሮ የሚገኙባቸው በመኖሪያ አካባቢዎች ላይ በሶሪያ የተባበሩ ታጣቂዎች የተፈፀሙ መደዳ ጥቃቶችን የሚያሳይ አስደንጋጭ ያለው ማስረጃ እንዳለውም አመነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል፡፡

ከማስረጃዎቹ መካከል የሶሪያ ብሄራዊ ጦር አካል የሆነው አህራር አል ሻርቂያ የሚባል ታጣቂ ቡድን አባላት ሃርቪን ኻላፍ በሚባሉ ታዋቂ የኩርድ ሴት ፖለቲከኛ ላይ የፈፀሙት አስከፊ ግድያ ማስረጃም እንዳለው የመብቶች ተሟጋቾች ቡድን አመልክቷል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG