በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሊብያ የሚገኙ ስደተኞችንና ፍልሰተኞችን በተመለከተ የአውሮፓ ሕብረትን ወቀሰ

በሊቢያ በፍልሰተኞች ላይ የሚደረግን ወከባና ሰቆቃ በመቃወም በስቶኮልም ስዊድን የተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ
በሊቢያ በፍልሰተኞች ላይ የሚደረግን ወከባና ሰቆቃ በመቃወም በስቶኮልም ስዊድን የተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ

የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች፣ ከሊብያ የሚነሱ ስደተኞችና ፍልሰተኞች የሜዲትራንያን ባሕር እንዳያቋርጡ በማድረግ፣ ለወከባና ለሰቆቃ እንዲዳረጉ ምክንያት ሆነዋል ሲል፣ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች፣ ከሊብያ የሚነሱ ስደተኞችና ፍልሰተኞች የሜዲትራንያን ባሕር እንዳያቋርጡ በማድረግ፣ ለወከባና ለሰቆቃ እንዲዳረጉ ምክንያት ሆነዋል ሲል፣ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

አምነስቲ ትናንት ማክሰኞ ይፋ ባደረገው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የአውሮፓ መንግሥታት ለሊብያ የቴክኒክ ዕገዛ በማድረግ ጭምር እየተባበሩ ናቸው።

በዚህም በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞችና ስደተኞች ዕጣ ፈንታ፣ በሊብያ ባለሥልጣናት፣ ሚሊሻዎችና ታጣቂዎች እጅ ውስጥ ነው ሲል፣ አምስቲ አመልክቷል።

የአምነስቲ አውሮፓ ዳይሬክተር ጆን ዳለሁሴን ሲናገሩም፣ ለተቀነባበረ ወከባና የመብት ጥሰት የተጋለጡ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች፣ እስር ቤት ውስጥ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግቶባቸው እንደሚገኙም አመልክተዋል።

ዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት /አይኦኤም/ እንዳስታወቀው፣ በ2017 ባሕር አቋርጠው ወደ አውሮፓ የሚገቡ ፍልሰተኞችና ስደተኞች ቁጥር፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር፣ በ53% ቀንሷል ብሏል።

ከ166,000 አዲስ ገቢዎች መካከል፣ ወደ 70% ያህሉ ኢጣልያ መግባታቸውንም አይኦኤም አመልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG