ሊባኖስ ያሉት የቤት ሰራተኞች በሰራተኛ ህግ አይታቀፉም። ህጋዊ ፈቃድ የሚያገኙት “ካፋላ” በተባለው ከአሰሪዋቻቸው ጋር በሚደረግ የፍልሰት ሥምምነት መሰረት ነው። ሰራተኞቹቢጎዱና ቢንገላቱም እንኳን ካለ አሰሪዎቻቸው ፈቃድ ሊወጡ አይችሉም ይላል አምነስቲ ኢንተርናሽናል።
ስለሆነም የሊባኖስ መንግሥት “ካፋላ” የተባለውን የፍልሰት ሥርዓት አቁሞ ለፈላሽ ሰራተኞች ዋስታና እንዲሰጥ አምነስቲ ጥሪ አድርጓል።
ሊባኖስ ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች የሆኑ ከአፍሪካና ከእስያ የሄዱ 250,000 ሺህ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ሰራተኞች መኖራቸውን አምነስቲ አውስቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ