በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ያልተቋጨው ውዝግብ፦ የመሳሪያ ባለቤትነት መብትና ኃላፊነት በዩናይትድ ስቴትስ


የዩናይትድ ስቴትስ በመሳሪያ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለማስታወስ የተሰራውን መታሰቢያ ጎብኝዎች ፎቶ ግራፍ ሲያነሱ
የዩናይትድ ስቴትስ በመሳሪያ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለማስታወስ የተሰራውን መታሰቢያ ጎብኝዎች ፎቶ ግራፍ ሲያነሱ

በዩናይትድ ስቴትስ ብዙዎችን ዒላማ ያደረጉ ግድያዎች ባልተቋረጡበት፡ አሜሪካውያን እነኝህን ፍጅት የሚያደርሱ ጥቃቶች ለመቀነስ እና አልፎ-አልፎ ከሚታዩት የተናጠል ድርጊቶች መለየት የሚቻልባቸውን መንገዶች አስመልክቶ ላይ አሁንም በብርቱ እንደከፋፈሉ ነው። በጦር መሳሪያ በሚፈጽሙ ጥቃቶች ሳቢያ በዩናይትድ ስቴትስ በየዓመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2017 ፒው የምርምር ማዕከል ያደረገው ጥናት እንዳመለከተው ከጠቅላላው ሕዝብ ከ40 ከመቶ በላይ የሚደርሱት አሜሪካውያን በቤታቸው ጠብመንጃ አለ።የመብት ተሟጋቾች እንደሚያስረዱት የጠብመንጃ ባለቤትነት በሕገ-መንግስቱ የተደነገገ መብት ነው፡፡ በሁለት የተከፈሉትን ጽንፍ የያዙ አስተያየቶች በመጽሃፋቸው የተነተኑት የሎሳንጀለሱ የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጥኚ ዊንክለር እንዳስረዱት “ክፍተቱን መሙላት” በጣም ከባድ ነው።

ይሁን እንጂ የየግዛት መንግስታት በተናጠል ጥብቅ ደንብና ገደቦችን ተግባራዊ አድርገዋል። ደራሲ እና ተንታኙ ዴቪድ ሄሜንዌይም በመሳሪያ አማካኝነት የሚፈጸሙ ጥቃቶች በህብረተሰብ ጤና ላይ እንደተጋረጡ ችግሮች መወሰድ አለባቸው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ያልተቋጨው ውዝግብ፦ የመሳሪያ ባለቤትነት መብትና ኃላፊነት በዩናይትድ ስቴትስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:15 0:00


XS
SM
MD
LG