ደሴ —
ጦርነት ከተቀሰቀሰባቸው የሰሜን ወሎና ዋግኽምራ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ሴቶችና ሕጻናት ከፍተኛ ተጎጅዎች መሆናቸውን በደሴ ከተማ ማረፊያ ካምፕ የተጠለሉ ተፈናቃዮች ገለጹ፡፡
ተፈናቃዮቹ በመንገድ ላይ የወለዱ መኖራቸውን ይናገራሉ፡፡
በሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ አካባቢ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በርካታ ኪሎ ሜትሮችን በእግራቸው አቆራርጠው ትራንስፖርት እስከሚገኝበት ከተማ ከዘለቁ በኋላ ወደ ደሴ ከተማ የሚገቡት ተፈናቃዮች ቁጥር በየቀኑ እያሻቀበ መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተለው የመንግሥት አካል እየገለጸ ነው፡፡
በአራት ት/ቤቶች ውስጥ እንዲያርፉ የተደረጉት ተፈናቃዮች አሁን ከስምንት በላይ ማረፊያ ካምፖች አስፈልጓቸዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡