በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል ግጭት የ12ኛ ክፍል ፈታኝ መምህራን ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ለመመለስ እንደተቸገሩ ተገለጸ


በዐማራ ክልል ግጭት የ12ኛ ክፍል ፈታኝ መምህራን ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ለመመለስ እንደተቸገሩ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:33 0:00

በዐማራ ክልል ግጭት የ12ኛ ክፍል ፈታኝ መምህራን ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ለመመለስ እንደተቸገሩ ተገለጸ

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት፣ በዐማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ መምህራን፣ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት በመቆሙ፣ ወደየአካባቢያቸው መመለስ እንዳልቻሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ፡፡

አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ መምህር፣ በክልሉ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መመደባቸውን ተናግረው፣ አሁን ግን፣ እርሳቸውና ሌሎች ባልደረቦቻቸው፣ ከዚያ መውጣት እንዳልቻሉና ለደኅንነታቸውም እንደሚሰጉ ተናግረዋል፡፡ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችም፣ ከክልሉ መውጣት ካልቻሉ የተቋማቱ ባልደረቦች ጋራ በስልክ እየተገናኙ እንደኾነ ተናግረው፣ ስለ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋራ እየተነጋገሩ እንደኾኑ ገልጸዋል፡፡ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ፣ ፈታኝ

መምህራንን ቀደም ብሎ እንዳስወጣ ገልጾ፣ ወደየመጡበት መመለስ ያልቻሉ ተማሪዎች ግን እንዳሉት አመልክቷል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከዐማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡

ዝርዝርን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG