በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥታዊ መዋቅር የፈረሰባቸው አንዳንድ የጎጃም አካባቢዎች በባህላዊ ሥርዐት እየተመሩ እንደኾነ ገለጹ

መንግሥታዊ መዋቅር የፈረሰባቸው አንዳንድ የጎጃም አካባቢዎች በባህላዊ ሥርዐት እየተመሩ እንደኾነ ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00

መንግሥታዊ መዋቅር የፈረሰባቸው አንዳንድ የጎጃም አካባቢዎች በባህላዊ ሥርዐት እየተመሩ እንደኾነ ገለጹ

በዐማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ መንግሥታዊ መዋቅሮች የፈረሱባቸው አንዳንድ የምሥራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ነዋሪዎች፣ ለፍትሕ እና ለሌሎች አገልግሎቶች ወደ ባህላዊ ሥርዐት እንደተመለሱ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት፣ የቀበሌ አስተዳደሮች፣ የፖሊስ ጣቢያዎች እና የፍትሕ ተቋማት ባለመኖራቸው ስርቆትን ጨምሮ ወንጀሎች እየተስፋፉ ነው።

በተለይ፣ በአንዳንድ ከተሞች፣ የፍትሕ ተቋማት ሥራ ላይ ባለመኾናቸው፣ ግጭቶችን በባህላዊ ሽምግልና እየተፈቱ እንደኾነ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ግድያ እና ከባድ ዘረፋ ሲፈጸም ግን፣ ፍትሕ ማግኘት እንደማይቻል አስረድተዋል።

በአገር ውስጥ የብዙኀን መገናኛ የተጠቀሱት የዐማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በበኩላቸው፣ በዐዲስ መልክ የተደራጀውን የጸጥታ እና የፖለቲካ መዋቅር፣ በራሱ እንዲቆም የማስቻል ሥራ እየተሠራ እንደኾነ አስታውቀዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG