በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭት ውስጥ ከዐማራ ክልል ወደ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ተማሪዎች “የታናናሾቻችን ዕጣ ፈንታ ያሳስበናል” አሉ

በግጭት ውስጥ ከዐማራ ክልል ወደ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ተማሪዎች “የታናናሾቻችን ዕጣ ፈንታ ያሳስበናል” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:11 0:00

በግጭት ውስጥ ከዐማራ ክልል ወደ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ተማሪዎች “የታናናሾቻችን ዕጣ ፈንታ ያሳስበናል” አሉ

በዐማራ ክልል፣ በአብዛኛው አካባቢ ያሉት ትምህርት ቤቶች፣ የዘመኑን የመማር ማስተማር ሒደት እንዳልጀመሩ የገለጹና ከክልሉ ወደ ዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ተማሪዎች፣ በተለይ፣ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ዕጣ ፈንታ እንደሚያሳሰባቸው ተናገሩ፡፡

ከመጡባቸው አካባቢዎች ያሉት ትምህርት ቤቶች፣ ላለፉት ሦስት ወራት እንደተዘጉ መኾናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹት ተማሪዎቹ፣ ከትምህርት ገበታ የራቁት ታናናሾቻቸው፣ ከዚኽ በኋላ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ዕድላቸው ሊጠብ እንደሚችል ስጋት እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት(ዩኒሴፍ)፣ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ በተከሠቱ ግጭቶች እና በተለያዩ አደጋዎች ምክንያት፣ 7ነጥብ6 ሚሊዮን ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደኾኑ አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG