በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል ግጭት ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ አልባ እንደሆኑ ተጠቆመ


በአማራ ክልል ግጭት ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ አልባ እንደሆኑ ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:53 0:00

በአማራ ክልል ግጭት ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ አልባ እንደሆኑ ተጠቆመ

በአማራ ክልል፣ ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ሳቢያ ሥራ ዐጥ እንደኾኑ የገለጹ ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ እንዳልቻሉ ተናገሩ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ከሥራ ውጭ የኾኑ ዜጎች፣ በግጭቱ ምክንያት ይሠሩባቸው የነበሩ ተቋማት በመዘጋታቸው፣ ካለፉት ሰባት ወራት ወዲህ ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንደተጋለጡ አመልክተዋል፡፡

በግጭቱ ምክንያት ከ1ሺ200 በላይ በኾኑ ኢንዱስትሪዎች ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ከሥራ ገበታ ውጭ እንደኾኑ፣ የአማራ ክልል የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡ ይህም፣ “በክልሉ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል፤” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG