በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሸዋሮቢት እና አካባቢው ግጭት ሰዎች እንደተገደሉና መንግሥታዊ ሥራዎች እየታጎሉ እንደኾነ ነዋሪዎች ገለጹ


በሸዋሮቢት እና አካባቢው ግጭት ሰዎች እንደተገደሉና መንግሥታዊ ሥራዎች እየታጎሉ እንደኾነ ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:33 0:00

በሸዋሮቢት እና አካባቢው ግጭት ሰዎች እንደተገደሉና መንግሥታዊ ሥራዎች እየታጎሉ እንደኾነ ነዋሪዎች ገለጹ

በዐማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ እና አካባቢው፣ ከትላንት በስቲያ ጀምሮ፣ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ እንዳለና ቢበዛ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ፣ የከተማዪቱ ነዋሪዎች ገለጹ።

የሟቾቹን ቁጥር፣ ከነዋሪዎቹ በስተቀር ከሌላ ወገን ማረጋገጥ አልተቻለም። በከተማዪቱ እና አካባቢዋ፣ “ፋኖ” በተባለው የዐማራ ክልል የታጠቁ ወጣቶች አደረጃጀት እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ግጭት እንደነበር ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

በግጭቱ ሳቢያ፣ መደበኛ መንግሥታዊ ሥራዎች እስከ መቋረጥ እየደረሱ ነው፤ ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

የዐማራ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊን አቶ ደሳለኝ ጣሰውን፣ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም፡፡

ይኹን እንጅ፣ በሰኔ ወር መጨረሻ፣ በባሕር ዳር ከተማ፣ የክልሉን ወቅታዊ የሰላም እና የደኅንነት ይዞታ አስመልክቶ በተካሔደ ግምገማ፣ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሩ በድንገት የተከሠተ ሳይኾን፣ ለዘመናት የተሰበከው የልዩነት ሐሳብ ውጤት ነው፤ የሚል መግባቢያ ላይ መደረሱን፣ በክልሉ መንግሥት የሚደገፈው የዐማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቦ ነበር፡፡

በዚኹ ወቅት፣ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊው፡- የክልሉ ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች፥ ለክልሉ ሰላም መከበር እና የሕግ የበላይነት መረጋገጥ፣ በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አስተላልፈው ነበር፡፡ በመከላከያ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዲሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፣ ተያያዥነት ባለቸው የጸጥታ እና የሰላም ጉዳዮች ላይ፣ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጸውልናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG