በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፋኖ ታጣቂንና የመከላከያ ሠራዊትን ግጭት በእርቅ ለመፍታት ጥረት ተጀምሯል


የፋኖ ታጣቂንና የመከላከያ ሠራዊትን ግጭት በእርቅ ለመፍታት ጥረት ተጀምሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:23 0:00

የፋኖ ታጣቂንና የመከላከያ ሠራዊትን ግጭት በእርቅ ለመፍታት ጥረት ተጀምሯል

በፋኖ ታጣቂ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል የተፈጠረውን ግጭት በእርቅ ለመፍታት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ በዐማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ አካባቢ ተቀስቅሶ የነበረው ጸጥታዊ ችግር በእርቅ እንዲፈታ፣ በሃይማኖት አባቶች እና በአገር ሽማግሌዎች በተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት ተፈትቶ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑ ተገለጸ፡፡

በአካባቢው፣ ከመከላከያ ሠራዊት ጋራ የተኩስ ልውውጥ ውስጥ ገብተው የነበሩት “የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ” በሚል የሚታወቁት ታጣቂዎች፣ በእርቁ ጥረት ውጊያ ማቆማቸውንና አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን፣ የአገር ሽማግሌዎች ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡

የሰሜን ምሥራቅ እዝ ምክትል አዛዥ፣ በአካባቢው ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም፣ የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች የተጫወቱትን ሚና ማድነቃቸውን፣ በክልሉ መንግሥት የሚተዳዳረው የዐማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጿል፡፡

ኮርፖሬሽኑ፣ “የምሥራቅ አማራ ፋኖ” ታጣቂ፣ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋራ የተደረገውን ሽምግልና ተቀብሎ ወደ መሰብሰቢያ ማዕከሉ(ካምፕ) ለመመለስግጭቱን በእርቅ መፍታቱንና ስለደረሰው ጉዳትም የተሰማውን ኀዘን መግለጹን በዘገባው አስደምጧል፡፡

በዚኽ ዙሪያ የተሰናዳውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን ፋይል ይጫኑ።

XS
SM
MD
LG