በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጎንደር ከባድ በተባለ ዐዲስ ውጊያ የከተማዋ እንቅስቃሴ እንደተስተጓጎለ ነው


በጎንደር ከባድ በተባለ ዐዲስ ውጊያ የከተማዋ እንቅስቃሴ እንደተስተጓጎለ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:04 0:00

በጎንደር ከባድ በተባለ ዐዲስ ውጊያ የከተማዋ እንቅስቃሴ እንደተስተጓጎለ ነው

በዐማራ ክልል ትልቋ ሁለተኛ ከተማ በኾነችው ጎንደር፣ ትላንት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂ ቡድን መካከል የተካሔደውን ግጭት ተከትሎ፣ የንግድ ድርጅቶች እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዛሬ ተዘግተው እንደዋሉ፣ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የዐይን እማኞች ጨምረው እንዳመለከቱት፣ ካለፈው ቅዳሜ ከሌሊቱ 9 ሰዓት አንሥቶ በከተማዋ ውጊያ መካሔዱን፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ለአሶስዬትድ ፕሬስ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎችም፣ ውጊያው “ከባድ” እንደነበር አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ወታደራዊ ማዘዣ፣ ትላንት ማምሻውን በሰጠው መግለጫ፣ “የጠላት ኃይል” ሲል የጠራው አካል፣ በአንድ የከተማዪቱ የፖሊስ ጣቢያ ላይ ማጥቃት እንደሰነዘረ አመልክቷል።

የፖሊስ ጣቢያውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተደረገ ነው በተባለ ወታደራዊ እንቅስቃሴ፣ ከ50 በላይ የሚኾኑ ታጣቂዎች እንደተገደሉና ቀሪው ከተማውን ለቆ እንደወጣ፣ ወታደራዊ ማዘዣው አስታውቋል።

በሌላ በኩል፣ በባሕር ዳር ከተማ፣ የፊታችን ጥቅምት ወር ሊካሔድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው ዓመታዊው የጣና ፎረም የመሪዎች ጉባኤ እንደተራዘመ፣ የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደኅንነት ጥናቶች ተቋም፣ ሰሞኑን በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ጉባኤው የተራዘመው “ባልተጠበቁ ኹኔታዎች ምክንያት” እንደኾነ የጠቀሰው ተቋሙ፣ “የጣና ቦርድ፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የጣና ሴክሬታሪያት በጥንቃቄ ከተወያዩ በኋላ” ውሳኔው እንደተላለፈ፣ ጽሕፈት ቤቱ በመግለጫው ላይ አመልክቷል።

ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG