በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ ሰላማውያን ሰዎች እየተጎዱ መኾኑን ነዋሪዎች ገለፁ


 በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ ሰላማውያን ሰዎች እየተጎዱ መኾኑን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:34 0:00

በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ ሰላማውያን ሰዎች እየተጎዱ መኾኑን ነዋሪዎች ገለፁ

የዐማራ ክልል ዋና መዲና ባሕር ዳርን ጨምሮ፣ በክልል የተለያዩ ሥፍራዎች፣ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ፣ ሰላማዊ ሰዎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት እየተዳረጉ እንደኾነ፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

ከባሕር ዳር አስተያየት የሰጡን ነዋሪዎች፣ በተኩስ ልውውጡ የተገደሉ ነዋሪዎችን፣ ማኅበረሰቡ እየቀበረ ነው፤ ብለዋል፡፡

የባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ምንጮችም፣ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተጎድተው፣ ወደ ሆስፒታሉ እየገቡ እንደኾነ ጠቁመዋል፡፡

በተያያዘ፣ ባለፈው ሳምንት፣ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመከላከያ ሠራዊቱ መካከል ግጭት በመቀስቀሱ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ወደ ክልሉ ኹሉም የአውሮፕላን ማረፊያዎች የሚያደርጋቸውን በረራዎች እንደሰረዘ፣ በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ)፣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ በዐማራ ክልል ለተፈጠረው የጸጥታ መደፍረስ፣ ገዢውን ፓርቲ ብልጽግናን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

መንግሥት እና ገዢው የብልጽግና ፓርቲ፣ “ጽንፈኛ እና ዘራፊ” የሚሏቸውን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች፣ ለችግሩ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG