በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተኩስ ልውውጥ ከቆመ በኋላ በሚካሔዱ የሲቪሎች ግድያ ነዋሪዎች መከላከያን ወቀሱ


የተኩስ ልውውጥ ከቆመ በኋላ በሚካሔዱ የሲቪሎች ግድያ ነዋሪዎች መከላከያን ወቀሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:49 0:00

የተኩስ ልውውጥ ከቆመ በኋላ በሚካሔዱ የሲቪሎች ግድያ ነዋሪዎች መከላከያን ወቀሱ

በዐማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ አካባቢ፣ ካለፉት ሦስት ቀናት ጀምሮ፣ በመከላከያ ኀይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፣ የንጹሐን ሕይወት ማለፉን አስተያየት ሰጭዎች ተናገሩ፡፡

በሁለቱም አካባቢዎች የሚደረገው የተኩስ ልውውጥ፣ ዛሬም ድረስ እንደዘለቀ መኾኑን፣ አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በንግድ ሥራ የሚተዳደሩ አንድ የአጣዬ ከተማ ነዋሪ፣ የተኩስ ልውውጡ ከቆመም በኋላ፣ ንጹሐን ይገደላሉ፤ ሲሉ፣ የመከላከያ አባላትን ይወቅሳሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ እስከ አሁን ከመንግሥት የተሰጠ ቀጥተኛ ምላሽ ባይኖርም፣ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ፣ ከሳምንታት በፊት ከደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ጋራ ባደረጉት ሕዝባዊ ውይይት፣ ከተልእኮው ውጭ የሚንቀሳቀስ የመከላከያ አባል ካለ ርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረው ነበር፡፡

በሌላ በኩል፣ የመራዊ ከተማ አስተያየት ሰጭ፣ ከተኩስ ልውውጡ በላይ፣ ከርቀት በሚወረወሩ ከባድ መሣሪያዎች ጉዳት እየደረሰብን ነው፤ ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ከትላንት በስቲያ፣ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በክልሉ ለወራት በቀጠለው ግጭት፡- ሰዎች በድሮን ስለመገደላቸው፣ የፋኖ ታጣቂዎችን ትደግፋላችኹ፤ በሚል፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከፍርድ ውጭ ግድያዎች ስለመኖሩ፣ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት ሓላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እና እገታዎች እየተፈጸሙ ስለመኾናቸው አብራርቷል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG