በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል በግጭቱ ሳቢያ የብዙ ኢንዱስትሪዎች ሥራ መታጐሉ ተጠቆመ


በዐማራ ክልል በግጭቱ ሳቢያ የብዙ ኢንዱስትሪዎች ሥራ መታጐሉ ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:26 0:00

በዐማራ ክልል በግጭቱ ሳቢያ የብዙ ኢንዱስትሪዎች ሥራ መታጐሉ ተጠቆመ

በዐማራ ክልል ካለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ጀምሮ የተስፋፋውን ግጭት እና አለመረጋጋት ተከትሎ፣ በምዕራብ እና በምሥራቅ ጎጃም እንዲሁም በደብረ ብርሃን የሚገኙ፣ ከ1ሺሕ216 በላይ ኢንዱስትሪዎች ሥራ እንዳቆሙ፣ የዐማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡

የክልሉ የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመት ቢሮ ሓላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ኢንዱስትሪዎቹ ሥራ ያቆሙት፥ በመንገድ መዘጋት፣ በኢንተርኔት ትይይዝ እና በስልክ መቋረጥ ነው፡፡

የኢንዱስትሪዎቹ ከሥራ ውጭ መኾን፣ በክልሉ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚዊ እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ተጽእኖ እየፈጠረ እንደኾነ፣ ሓላፊው አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም፣ በግጭቱ በወደሙት በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች ምክንያት፣ ለሥራ ዐጥነት የተዳረጉ በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች፣ በከፍተኛ ችግር ላይ እንደወደቁ አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG