በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በባሕር ዳር ከተማ ወላጆች በደህንነት ሥጋት ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት እየላኩ እንዳልሆነ ገለጡ


የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ
በባሕር ዳር ከተማ ወላጆች በደህንነት ሥጋት ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት እየላኩ እንዳልሆነ ገለጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:31 0:00

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አርብ በከተማዋ በሚገኝ ትምህርት ቤት የተከሰተውን የቦምብ ፍንዳታ ተከትሎ ሥጋት የገባቸው የባሕር ዳር ከተማ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እየላኩ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም አቤ፣ ባለፈው አርብ በአድቬንቲስት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈፀመ ጥቃት አንድ መምህርና ሁለት ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ ትላንትና ዛሬ በከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ገብተው የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር መቀነሱን አክለው ገልጸዋል።

ሆኖም “ትምህርት ቤቶች በፀጥታ ኅይል እንዲጠበቁ ውሳኔ በመተላለፉ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲልኩ” በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG