በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተመራው ልዑክ ዋሺንግተን ዲሲ ገብቷል


በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ
በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ በዩናይትድ ስቴትስ የሚያደርገውን ጉብኝት በመጀመር ዛሬ ጠዋት ዋሺንግተን ዲሲ ገብቷል።

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ በዩናይትድ ስቴትስየሚያደርገውን ጉብኝት በመጀመር ዛሬ ጠዋት ዋሺንግተን ዲሲ ገብቷል።
በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራው ልዑክ ሲገባ ብዛት ባላቸው ኢትዮጵያውያን አቀባበል ተደርጎለታል።
የጉዞው ዓላማ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአማራ ልማት ላይ የራሳቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ለማድረግ ነው ተብሏል።
እንዲሁም ለውጡን ተከትሎ በክልሉ መንግሥት አቋም ላይ በመወያየት በቀጣይ ሥራዎች ላይ አብሮ ለመሥራት ያለውን መልካም አጋጣሚ ማሳወቅም ሌላው ዓላማው መሆኑ ተገልጿል፡፡
ልዑኩ በሰሜን አሜሪካ በሚኖረው ቆይታ በተለያዩ ግዛቶች የአማራ ልማት ይመለከተናል ከሚሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG