በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከወልቃይትና ራያ አካባቢዎች ታፍነው የተወሰዱ ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ተገለፀ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በጦርነት የተሸነፈው ህወሓት ሲያስተዳድራቸው ከነበሩት ከወልቃይትና ራያ አካባቢዎች አፍኖ የወሰዳቸው በ10 ሽዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች የደረሱበት አለመታወቁን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።

በማይካድራ ንፁሃን ዜጎችን ጨፍጭፈው ወደ ሱዳን የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ያመሩ ወጣቶች በህግ እንዲጠየቁም ሁኔታዎችን እያመቻቸሁ ነው ብሏል የክልሉ መንግሥት።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ ታፍነው ተወስደዋል በተባሉ ንፁሀን ዜጎች ላይ መረጃው እንደደረሰውና በቀጣይ እንደሚያጣራ ገልጿል።

በማይካድራ የተጨፈጨፉ ዜጎች ቁጥር እንደሚጨምርም ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ከወልቃይትና ራያ አካባቢዎች ታፍነው የተወሰዱ ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:41 0:00


XS
SM
MD
LG