በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል ቋራ ወረዳ ሦስት ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ ሞቱ   


ፍቶ ፋይል፦ ጎንደር ከተማ
ፍቶ ፋይል፦ ጎንደር ከተማ

በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ልዩ ስሙ "በርሚል ጊዮርጊስ" በተባለ የፀበል ስፍራ እንደገና ባገረሸው የኮሌራ ወረርሽኝ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል::

የተቋሙ ዳሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት ካለፈው ታኅሣሥ መጨረሻ ጀምሮ፣ በፀበል ስፍራው ወረርሽን ሦስት ሰዎች ሲሞቱ ከ200 በላይ የሚኾኑ ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተው በጤና ተቋማት ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

እስከ ትላንት ድረስ በየቀኑ የበሽታው ተጠቂ በጤና ተቋማት እየተመዘገበ እንደሚገኝ የገለፁት ዳይሬክተሩ የፀበል ስፍራው በትንሹ ለ30 ቀናት ካልተዘጋ ወረርሽኙ ከክልሉ አልፎ በሀገር ከፍተኛ ደረጃ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ቋራ ወረዳ ሦስት ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ ሞቱ   
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:11 0:00

ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ፀበሉ ለሚመጡ ፀበልተኞች የጥንቃቄ መልዕክት ለማስተላለፉ የጤና ባለሞያዎች፣ ችግር እንደገጠማቸው የገለፁት አቶ በላይ የፀበሉ አጥማቂዎች መልዕክቱ እንዲተላለፉ ብዙም ትብብር እያሳዩ አይደለም ብለዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቆሞስ ኃይለማርያም ያሳይ፣ “የጤና ባለሞያዎች ወረርሽኙ አሳሳቢ ነው ፀበሉ መዘጋት አለበት ካሉ እንዘጋለን” ብለዋል

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG