በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል የቀድሞ ፖሊስ ኮሚሽነር አረፉ


አበረ አዳሙ
አበረ አዳሙ

የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በድንገተኛ ህመም ማረፋቸውን ኮሚሽኑ ገለፀ። የኮሚሽነር አበረ አዳሙ ዜና እረፍት የተሰማው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሲሆን አስከሬናቸው ለምርምራ ወደ አዲስ አበባ መላኩንም የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ገልፀዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን ከሁለት ዓመት በላይ በኮሚሽነርነት ያገለገሉትና ባሳለፍነው ሳምንት ከሥልጣናቸው የተነሱት ኮሚሽነር አበረ ያረፉት በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በህክምና እየተረዱ በነበረበት ወቅት መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳሬክተር ኮማንደር መሠረት ደባልቄ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG