በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሸባሪ ያሏቸውን ታጣቂ ቡድኖች በጋራ ጥረት ለመከላከል እንደሚሠሩ የአማራ እና የኦሮምያ ክልሎች አስታወቁ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ ከተማ

የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ከሰሞኑ በኦሮምያ ክልል በንጹኃን ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ ሁለቱን ክልሎች በመለያየት ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ነው ብለውታል፡፡

መሰል ድርጊት እንዳይፈጸም እና መንግሥት ሸኔ የሚለውን፣ ራሱን ደግሞ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሚለውን ቡድን ለማጥፋት ሁለቱ ክልሎች በትብብር መስራት እንዳለባቸውም ርዕሰ መስተዳድሮቹ አብራርተዋል፡፡

ይህን የሁለቱን ክልሎች እርምጃ በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡን የኦፌኮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፣ እርምጃው አሁን ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ ሊያባብስ ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው ሲገልጹ የአዴኃን ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን አለምነህ ደግሞ ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:58 0:00

XS
SM
MD
LG