በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጃን አሞራ ወረዳ በረኀብ ምክንያት ከ12ሺሕ በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋረጡ


በጃን አሞራ ወረዳ በረኀብ ምክንያት ከ12ሺሕ በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋረጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00

በጃን አሞራ ወረዳ በረኀብ ምክንያት ከ12ሺሕ በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋረጡ

በዐማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በጃን አሞራ ወረዳ፣ ዘንድሮ በተከሠተው ድርቅ ምክንያት፣ ከ12ሺሕ በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ተገለጸ፡፡

የወረዳው አስተዳዳሪ ተወካይ እና የትምህርት ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ሀብታሙ ኀይሉ፣ ዛሬ ኀሙስ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ በወረዳው በ38 ቀበሌዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች ይማሩ ከነበሩት ከ17ሺሕ በላይ ተማሪዎች ውስጥ፣ ዘንድሮ በትምህርት ገበታቸው የተገኙት፣ አምስት ሺሕ ያህሉ ብቻ እንደኾኑ አስታውቀዋል፡፡

ዋናው የችግሩ መንሥኤ፣ በአካባቢው የተከሠተው ድርቅ እና በዚኽም ሳቢያ፣ ወላጆች የትምህርት ቁሳቁስ ለልጆቻቸው ማሟላት አለመቻላቸው እንደኾነ፣ አቶ ሀብታሙ አስረድተዋል፡፡

ያነጋገርናቸው የተማሪዎች ወላጆች በበኩላቸው፣ ልጆቻቸውን በባዶ ሆዳቸው ረጅም መንገድ ተጉዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዲሔዱ አለመፈለጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በረኀብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ የራቁ ተማሪዎችም፣ ለስደት እንደተዘጋጁ አመልክተዋል፡፡

የርዳታ እህል ወደ ወረዳው መላኩን ያስታወቀው የክልሉ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በበኩሉ፣ ባለው የጸጥታ መደፍረስ የተነሣ ለችግረኞች ለማዳረስ እንዳልተቻለ ገልጿል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG