በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋግኽምራ ዞን በረኀብ ተጨማሪ ዜጎች እንደሞቱና ሊከፋም እንደሚችል ተጠቆመ


በዋግኽምራ ዞን በረኀብ ተጨማሪ ዜጎች እንደሞቱና ሊከፋም እንደሚችል ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:16 0:00

በዋግኽምራ ዞን በረኀብ ተጨማሪ ዜጎች እንደሞቱና ሊከፋም እንደሚችል ተጠቆመ

በዐማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ቢላዛ ቀበሌ፣ ባለፉት አራት ቀናት ውስጥ፣ በረኀብ የተጎዱ ተጨማሪ ሰዎች እንደሞቱ፣ የአካባቢው ባለሥልጣን አስታወቁ፡፡

የቀበሌው አስተዳዳሪ አቶ ማለደ ብሬ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በ2015/16 የመኸር ዘመን በአካባቢው የተከሠተው ድርቅ ባስከተለው ረኀብ፣ ቀደም ሲል ስድስት ሰዎች እንደሞቱ አውስተው፣ ባለፉት አራት ቀናት ውስጥ፣ ይህ ቁጥር ወደ ስምንት ከፍ እንዳለ ገልጸዋል፡፡

በቀበሌው ረኀቡ እየከፋ ከመምጣቱ የተነሣ፣ ከዚኽ ቀደም የርዳታ እህል የሚጓጓዝባቸው አህዮችም ሳይቀሩ፣ በመኖ እጥረት ዐቅማቸው እንደደከመና ርዳታው ቢገኝ እንኳን ወደ ቀበሌው ማድረሱ ሌላው ፈተና እንደኾነ፣ አቶ ማለደ አክለው አመልክተዋል፡፡

በክልሉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ የሻምበል ዋለም፣ ሰሞኑን ወደ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ሊላክ የነበረውና ባሕር ዳር ከተማ ላይ እንደቆመ የዘገየው የርዳታ እህል፣ በመንገድ እና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት ወደ ሰሜን ጎንደር ዞን እንደተላከ አስታውቀዋል፡፡

የክልሉ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽንም፣ 40 በመቶ የርዳታ እህል በጸጥታ ችግር ምክንያት ለማሰራጨት እንዳልተቻለ፣ ባለፈው ሳምንት ለአሜሪካ ድምፅ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG