በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእገታ ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የአማራ ክልል ፖሊስ አስታወቀ


የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ
የእገታ ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የአማራ ክልል ፖሊስ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:18 0:00

በአማራ ክልል፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት እየጨመረ የመጣው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸም የእገታ ወንጀል ‘ከአሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል’ መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በኮሚሽኑ የሚዲያ ጉዳዮች ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር መሳፍንት እሸቴ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ባለፈው አመት ብቻ ከ287 በላይ የእገታ ወንጀሎች ተፈፅመዋል።

በክልሉ ውስጥ የተፈጠሩ ግጭቶችን ለእገታው ወንጀል መጨመር እንደ ምክንያት ያነሱት፣ ኮማንደር መሳፍንት መረጃው ለፖሊስ ያመለከቱትን ብቻ ስለሚያካትት ትክክለኛ ቁጥሩ ከተጠቀሰው በእጅጉ ይልቃል በማለትም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ በበኩላቸው መንግስት በአንዳንድ የፀጥታ ኃይል አባላትና በሌሎች ቡድኖች የሚፈጸመውን የእገታ ወንጀል መቆጣጠር አለበት ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG