በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እርቅ የፈጸሙ የቅማንት ታጣቂዎች እንደታሰሩ የቅማንት ኮሚቴ አስታወቀ


እርቅ የፈጸሙ የቅማንት ታጣቂዎች እንደታሰሩ የቅማንት ኮሚቴ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:38 0:00

እርቅ የፈጸሙ የቅማንት ታጣቂዎች እንደታሰሩ የቅማንት ኮሚቴ አስታወቀ

የዐማራ ክልል መንግሥት ያደረገውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው፣ ከትጥቃዊ ትግል ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስን መርጠው እርቅ ከፈጸሙ የቅማንት ታጣቂዎች መካከል፣ ከ100 በላይ የሚኾኑቱ መታሰራቸውን፣ አንድ የቅማንት የማንነት እና የራስ አስተዳደር አስመላሽ ኮሚቴ አባል ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

የማኅበሩ አባል መኾናቸውን በስልክ የተናገሩት አቶ አንዳርጌ ሞላ፣ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል፤ በሚል፣ በእስር ላይ የሚገኙ 127 ግለሰቦች፤ የተጠረጠሩበት እና የተከሠሡበት ወንጀል አግባብነት እንደሌለው ተናግረዋል።

የአማራ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፣ 100 ሰዎች በሕግ ቁጥጥር ሥር መኾናቸውን ገልጸው፣ እነርሱም በአካባቢው በነበረው ግጭት ከባድ ወንጀል በመፈጸም ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተናግረዋል።

በአካባቢው እንደሚኖሩ የነገሩን አንድ የሀገር ሽማግሌ በበኩላቸው፣ እርቀ ሰላሙ ከወረደ በኋላ፣ በአካባቢው ሰላም መስፈኑንና ኹለቱ ሕዝቦች፣ ገበያም ኾነ ለቅሶ በጋራ እየዋሉ እንዳለ ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG