በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዐማራ ክልል ግጭት ሠራተኛውን ዋስትና እያሳጣው እንደኾነ ኮንፈዴሬሽኑ አስታወቀ


የዐማራ ክልል ግጭት ሠራተኛውን ዋስትና እያሳጣው እንደኾነ ኮንፈዴሬሽኑ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00

የዐማራ ክልል ግጭት ሠራተኛውን ዋስትና እያሳጣው እንደኾነ ኮንፈዴሬሽኑ አስታወቀ

በዐማራ ክልል በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት፣ የቀጣሪ ድርጅቶች ሥራ እንደተስተጓጎለ ያስታወቁት፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፈዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ ሠራተኞች እንደተበተኑና በሥራ ላይ ካሉትም፣ እስከ ሦስት ወራት ድረስ ደመወዝ የማይከፈላቸው ሠራተኞች እንዳሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልልም በቀጠለው ግጭት እንዲሁ፣ ሠራተኛው የተለያዩ ችግሮች እየደረሱበት እንደኾነ ያመለከቱት አቶ ካሳሁን፣ ኹኔታው የሠራተኛውን ሕይወት አክብዶታል፤ ብለዋል፡፡

በዐማራ ክልል፣ ከግል ድርጅቶች ከሥራ የተሰናበቱ ሠራተኞች በበኩላቸው፣ የቀን ገቢያቸው እንደተቋረጠ ጠቅሰው፣ አስቸጋሪ ሕይወት እየመሩ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጠን፣ አንድ የሠራተኞች መብት ተሟጋች ድርጅትም፣ በሥራ ላይ ያለው የአሠሪ እና ሠራተኛ ዐዋጅ፣ በቀውስ ጊዜ ለሠራተኞች በቂ ጥበቃ እንደማያደርግ ተችቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG