በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ርዕሰ መስተዳድሩ አነጋገሩ፤ እንዲመለሱ ጠየቁ


የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር

የክረምቱ እርሻ ጊዜ ሳይጠናቀቅ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተፈናቅለው የመጡ የአማራ ተወላጆችን ቀድሞ ወደነበሩበት ቦታ ለመመለስ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

የተፈናቃዮቹን ፈቃድ መሰረት አድርጎ አስተማማኝ ሰላም በሰፈነባቸው አካባቢዎች ነው ተፈናቃዮቹ እንዲመለሱ ይደረጋል የተባለው፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ በሚገኘው ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ የሰፈሩ ተፈናቃዮችን ጎብኝተው ነበር፡፡

ተፈናቃዮቹ ከመንግሥትና ከህዝብ የተደረገላቸውን እገዛ አድንቀው በተወሰኑ ጊዜያት በሚሰፈርልን አነስተኛ ቀለብ ያለምንም ሥራ ከምንቆይ በዘላቂነት የምንቋቋምበት መንገድ ይመቻች የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ርዕሰ መስተዳድሩ አነጋገሩ፤ እንዲመለሱ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:24 0:00


XS
SM
MD
LG